ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
ስዕል:Eyob 6.jpg
                         ኢዮብ ስዩም ተፈሪ

ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በፊልም ፤ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እናስተዋውቃለን፡፡ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ5 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ከሚድያ ዘርፍ ታሪኩ የሚቀርብለትም ኢዮብ ስዩም ተፈሪ ነው፡፡

                       ልጅነትና ትምህርት
 

ኢዮብ ስዩም ተፈሪ የተወለደው አዲስ አበባ ሲሆን ዕድገቱ ሞጆ ከተማ ነው :: ወላጅ አባቱን ነፍስ ሳያውቅ በሞት የተነጠቀው ብላቴና የቄስ ትምህርትና የሕጻናት መዋያ ትምሕርቱን በአዲስ አበባ እንዲሁም :የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርቱን የተከታተለው ሞጆ ከተማ ነው ። ከ12 ኛ ክፍል ቦኋላ በአዋሳ መምህራን ትምሕርት ተቋም በመምሕርነት ሰልጥኗል :: ከዚያም በቋንቋና ስነጽሑፍ ዲፕሎማና ዲግሪ በማኔጅመንት ማስተርሱን ተምሯል :: ከተለያዩ የውጪ አገር ተቋማት የጋዜጠኝነትና ኮምዩንኬሽን ኮርሶችን ወስዷል ።

      ቤተሰባዊ ሁኔታ

የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ከማንኛውም ሠው ጋር በቀላሉ ተግባቢ ቁጡ የሚመስል ግን ነገሮችን ወዲያው የሚተው እንደሆነ በብዙዎች ይነገርለታል ።


           የሥራ ዓለም


በመጀመሪያ ለ10 የሥራ ዓመታት በሸንኮራና በምንጃር ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በመምህርነት ያገለገለ ሲሆን ወደ አዲስ አበባም በመምጣት በመምሕርነትና ለተለያዩ የህትመት ውጤቶች ጽሑፎቹን በመስጠት ሲሳተፍ ቆይቷል ።በተለይ ከ1996-1997 ዓመተምሕረት የታርጌት ሚዲያና ሕትመትን በማቋቋም ጋዜጣና መጽሔትን ማሳተም የጀመረ ሲሆን ወቅቱ በፈጠረው ፖለቲካዊ ትርምስ ለእስር ተዳርጎ እንደነበረም ይነገራል ::ከዚያ በኋላም በመምሕርነት ለተወሰነ ጊዜ ካገለገለ ቦኋላ በወቅቱ በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምሕርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኀበረቅዱሣን ከፍተኛ የሕትመት ቁጥር ባለው የስምዐጽድቅ ጋዜጣ ከሪፖርተርነት እስከ አዘጋጅነት እንዲሁም የሕዝብ ግንኙነት ኤክስፐርት እናም በዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ የመጀመሪያዋ የግቢ ጉባዔ (ጉባዔ ቃና) መጽሔት ዋና አዘጋጅ በመሆን አገልግሏል ::

ከዚያ በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያም በሸገር ኤፍኤም 102.1 የእሁድ እንደገና ፕሮግራም አዘጋጅ በመሆን የሠራ ሲሆን በኤዲስቴለር ትሬዲንግ በሚዘጋጀውና በፋና ኤፍኤም 98.1 በሚተላለፈው የአውቶሞቲቭ ጆርናል የሬዲዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ እንዲሁም በኢዲስቴለር ትሬዲንግ ምክትል ሥራ አሥኪያጅ በመሆን የአሐዱ ሬዲዮ መሥራች በመሆን ሠርቷል ። በመቀጠልም በፋና ኤፍኤም 98.1 ላይ አውቶሞቲቭ ታይም የሬዴዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅና የኦፍታጎን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ሥራአስኪያጅ በመሆን አገልግሏል ። በትራንስፖርት ባለሥልጣን የአገር አቀፍ ሚዲያ ፎረም ሰብሳቢ እንዲሁም በአገሪቱ በተሠሩ የባቡር ፕሮጀክት የሞጆ አዋሳ የፍጥነት መንገድ :የአዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የኢቨንት ኦርጋናይዚንግ ሥራውን ከጓደኞቹ ጋር ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ የሠራ ሁለገብ ባለሙያ ነው ::

ኢዮብ በማኀበራዊ ሱታፌው አሳዳጊ አልባ ሕጻናትን ለማገዝ ካለው የውስጥ ፍላጎት አንዲት ሴት ልጅ ወስዶ ልጁ አድርጓታል :: በአገሪቱ ያሉ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች በሚሸለሙበት የበጎ ሰው ሽልማት ውስጥ ከመነሻው ጀምሮ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ የተወጣ ሲሆን በተለያዩ ኃይማኖታዊ በዐላት ጠያቂ የሌላቸውን የሕግ ታራሚዎች ለረጂም ጊዜአት ኃይማኖት: ብሔር :ጎሳ ሳይለይ አቅም በፈቀደ ለበዐላት የሚሆኑ ቁሶችን ለማድረስ በመሞከሩ ይታወቃል :: በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂው ዘርፍ በተለይ በአገራችን እየገቡ ያሉትን ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጠቃሚዎች :ባለንብረቶችና :የቴክኒክ ሠዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ከ 1152 በላይ ፕሮግራሞችን በመስራት በሬዲዮ እንዲተላለፍ አድርጓል ። በኢትዮጵያ እጅግ አሳሳቢ የሆነውን የመኪና አደጋ ለመቀነስ የሚረዱ በርካታ ፕሮግራሞችን ሠርቷል ። አደጋን በቅድሚያ ለመከላከልና ለመኪኖች ደህንነት በመለዋወጫዎች ምክንያትም የሚባክነውን የውጪ ምንዛሪ ለማስቀረት በሚሠራቸው የአውቶሞቲቭ ፕሮግራሞች የተለያዩ የምስጋና ሰርተፍኬቶች ያገኘ ሲሆን በፎርድ አፍሪካ ጋባዥነት በተደጋጋሚ በደቡብ አፍሪካና ኬኒያ ሥልጠናዎችን ወስዷል፡፡ ኢዮብ ስዩም ሀሳቡን በነጻነት መግለጽ የሚወድ ለኢትዮጵያ ታሪክ ታላቅ ፍቅር ያለው ሲሆን በተለይ አንድ ስራ ከታሰበ እውን የማይሆንበት ምክንያት የለም ብሎ የሚያምን ሰው ነው፡፡Seyoumyordanoseyob @ gmail. Com