(Go: >> BACK << -|- >> HOME <<)

Jump to content

ከ«ሶቪዬት ሕብረት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 151 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q15180 ስላሉ ተዛውረዋል።
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 5 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q15180 ስላሉ ተዛውረዋል።
መስመር፡ 92፦ መስመር፡ 92፦
{{Link FA|no}}
{{Link FA|no}}


[[diq:Yewiya Sowyeti]]
[[ky:Кеңештик Социалисттик Республикалар Бирлиги]]
[[lij:Union de Repubbriche Soçialiste Sovietiche]]
[[ne:सोभियत संघ]]
[[pa:ਸੋਵੀਅਤ ਸੰਘ]]
[[uz:Shoʻro Sotsialistlik Jumhuriyatlari Ittifoqi]]
[[uz:Shoʻro Sotsialistlik Jumhuriyatlari Ittifoqi]]

እትም በ01:44, 22 ማርች 2013

Союз Советских Социалистических Республик
ሶዩዝ ሶቭየትስኪህ ሶትሲያሊቲቼስኪህ ሬስፑብሊክ
ሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ

1922-1991 እ.ኤ.አ.

የሶቪዬት ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ የሶቪዬት ሕብረት አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር የሶቪዬት ሕብረት ብሔራዊ መዝሙር
የሶቪዬት ሕብረትመገኛ
የሶቪዬት ሕብረትመገኛ
ሶቪዬት ሕብረት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኅሏ
ዋና ከተማ ሞስኮ
ብሔራዊ ቋንቋዎች መስኮብኛ እና ብዙ ሌሎች
መንግሥት
{{{
 
ዋና ቀናት
ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም.
ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ፲፱፻፰፬ ዓ.ም.
 
ምስረታ
መጨረሻ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
22,402,200
የሕዝብ ብዛት
የ1991 እ.ኤ.አ. ግምት
 
293,047,571
ገንዘብ የሶቪዬት ሩብል
የስልክ መግቢያ +7
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .su
የቀደመው የተካው

Russian SFSR
Transcaucasian SFSR
Ukrainian SSR
Belorussian SSR


ሩሲያ
ጂዮርጂያ
ዩክሬይን
ሞልዶቫ
ቤላሩስ
አርሜኒያ
አዘርባጃን
ካዛክስታን
ኡዝቤኪስታን
ቱርክሜኒስታን
ኪርጊዝስታን
ታጂኪስታን
ኤስቶኒያ
ሌትላንድ
ሊትዌኒያ

ሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ፲፱፻፲ ዓ.ም. የተከሰተውን የሩሲያ አብዮት ፍንዳታ፤ እንዲሁም ያንን ተከትሎ ለሦስት ዓመታት የተከናወነውን የሩሲያ «ውስጣዊ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት» ተከትሎ በስብአዊ ሕገ መንግሥት (socialist constitution) በአራት ሪፑብሊኮች ቅንብርነት የተመሠረተ አገር ነበር።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ከቀድሞው የናዚ ጀርመን እጅ የተወሰዱ አገሮችን በማቀላቀል እንዲሁም በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም በጉልበት ሌሎች የምሥራቅ አውሮፓ አገሮችን በመቀላቀል ሕብረቱ አሥራ ስድስት ሪፑብሊኮችን ያካተተ ነበር። በዘመን ቆይታና በጥንካሬም የጎለበተ ሕዝባዊ ዓብዮታዊ የሕብረት ሪፑብሊክ በመሆኑም በተለይ በ«ቀዝቃዛ ጦርነት» (cold war) በሚባለው በ«ምዕራብና በምሥራቅ» ዓለም ተከስቶ በነበረው ፍጥጫ ጊዜ፣ በዓለም ላይ ለሚመሠረቱ ሕዝባዊ መንግሥታት ዋና የሽከታ አርአያ የነበረ መንግሥት ነበር።

በ ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጀምሮ ይሄ ሕብረት እስከፈረሰበት እስከ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የ«ቀዝቃዛ ጦርነት» ዘመን የሶቪየት ሕብረት በዓለም ከነበሩት ሁለቱ ተቃራኒ ኃያላን መንግሥታት አንዱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ላይ በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም የተመሠረተውን የአብዮት ወታደራዊ የደርግ መንግሥት በጦር መሣሪያ፤ በአማካሪነት፤ በገንዘብ፤ ወዘተረፈ፤ ዋነኛ ደጋፊና ታላቅ ተዋናይ አገር ነበር።

በሕዝባዊ አብዮታዊ እንቅስቃሴ መነሻነት በኃይልና በፖለቲካ ሚዛናት በሰባ ዓመታት ውስጥ ዳብሮ በዓለም ከሁለቱ ኃያላን መንግሥታት አንዱ እስከመሆን የደረሰው የሶቪየት ሕብረት በዕድሜው መግቻ ዓመታት ላይ በዓለም የተከሰቱ ሁለት ዓቢይ ጉዳዮች ለፍጻሜው ዋና ምክንያቶች እንደነበሩ ይገለጻል።

ኬኔዝ ኤስ ዴፊይስ (Kenneth S. Deffeyes) “Beyond Oil” ላይ እንዳሰፈረው አንደኛው፤ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን ሳውዲ አራቢያ የነዳጅ ዋጋዋን እንድታወርድ በማበረታታቸው የሶቪዬት ሕብረት ከነዳጅ ሽያጥ የምታገኘውን ትርፍና የውጭ ምንዛሪ መጠን ክፉኛ ማመንመኑ፤[1] ሁለተኛ በሶቪዬት ሕብረት ሥልጣንን የተረከቡት ሚካይል ጎርባቾቭ በአገሪቱ ዱኛ [2](economy) እንዲሁም የኮሙኒስት አመራር ላይ ጥልቅ የሆኑ ፔሬስትሮይካ እና ግላስኖስት በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ሁለት ሥር ነቅናቂ ለውጦችን መትግበራቸው ነው።

ለምሳሌ የጎርባቾቭ የግላስኖስት ውጅማ [2](policy)፣ ከዚህ በፊት በአስተዳደሩ መሣሪያዎች ከሕዝቡ በምስጢርነት ይደበቁ የነበሩ መንግሥታዊ/ሰብአዊ፤ ወ.ዘ.ተ. መረጃዎችን ማንኛውም ዜጋ የማግኘት መብቱን ያረጋገጠለት አቢይ ውጅማ ሲሆን፤ የፔሬስትሮይካ ስልት ደግሞ ከአብዮቱ ጀምሮ የማዕከላዊው የኮሙኒስት ሸንጎ በቁልፍ እጅ ይዞት የነበረውን ስልጣን በማላቀቅ የቻራስፍና (democracy) ስርዐት በሕዝቡ አዕምሮ እንዲሰነጽ መንገድ የከፈተ ውጅማ ነው።

የቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት መጨረሻ ላይ ታሕሣሥ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ተደምስሶ በዓለም መንግሥታት እውቀትና ስምምነት ህጋዊ ወራሽነት የሩሲያ መንግሥት እንደሆነ ታወጀ። ሩሲያም በዚህ መሠረት የቀድሞውን የሶቪዬት ሕብረት የውጭ ዕዳዎች እንዲሁም የውጭ ንብረቶች በፈቃዱ ተቀበለ። በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ተፈርመው የነበሩም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም ሩሲያ መቀበሏን አስታውቃለች።

ዋቢ መጻሕፍት

  1. ^ Kenneth S. Deffeyes, Beyond Oil: The View from Hubbert's Peak.
  2. ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)፣ "ሰገላዊ አማርኛ"፤፳፻ ዓ.ም.

መለጠፊያ:Link FA