(Go: >> BACK << -|- >> HOME <<)

Jump to content

መጋቢት

ከውክፔዲያ
The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.

መጋቢት

የመጋቢት ቀናት
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30

መጋቢት የወር ስም ሆኖ በየካቲት ወር እና በሚያዝያ ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ሰባተኛው የወር ስም ነው።

«መጋቢት» ከግዕዙ ግስ «መገበ» ከሚለው ቃል የተባዛ ነው።[1]

አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ የመጋቢትን ትርጉም እንደዚህ አስቀምጠውታል፦ "የወር ስም፤ ፯ኛ ወር። ይኸውም ጌታ በጸሎተ ኀሙስ ለሐዋርያት ሥጋውንና ደሙን መመገቡንና ዐርብ በሠርክ ዲያብሎስን ሽሮ አዳምን ወደ ቀድሞ ማዕርጉ መመለሱን ያሳያል።" [2]

ቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ፓረምሃት ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከፈርዖን ስም «ፓ-ኤን-አመንሆተፕ» (የአመንሆተፕ ወር) መጣ።

ጎርጎርዮስ አቆጣጠርማርች መጨረሻና የኤፕሪል መጀመርያ ነው።

በመጋቢት ወር ነጻነታቸውን ያገኙ የአፍሪቃ አገራት



የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
  1. ^ "The Ethiopic Calendar". Archived from the original on 2014-03-31. በ2009-08-27 የተወሰደ.
  2. ^ ደስታ ተክለ ወልድ፤ “ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት”፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤትአዲስ አበባ (፲፱፻፷፪ ዓ/ም ገጽ ፯፻፵፮